የኮርፖሬት ምርምርና ልማት ማዕከል

ማዕከሉ በብ.ኢ.ኮ ስር እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ዲዛይን በማድረግ እንዲሁም የተሰሩትን ዲዛይኖች በማሻሻል ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ያለ ማዕከል ነው። በተለይም ሀገራችን የጀመረችውን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የግንባታ ዲዛይን በማሻሻል ከ5250 ወደ 6000 ሜጋ ዋት ከፍ እንዲል እንዲሁም 450 በመጨመር ወደ 6450 ከፍ እንዲል አድርጓል። በተጨማሪም ማዕከሉ የስኳር፣ የማዳበሪያና የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ዲዛይን በመስራትና የግንባታ ሂደቱ በዲዛይኑ መሰረት እንዲሰራ ክትትል ያደርጋል። በርካታ የኮሜርሺያልና ወታደራዊ ምርምሮች የሚደረግበት ተቋም ነው፡፡ ማዕከሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የዲዛይንና ሱፐርቪዥን ስራ በማከናወን አገራዊ የኢንጅነሪንግ ዲዛይን አቅም በተሻለ መገንባትን ዓላማ አድርጎ ለመስራት በሚያስችል መልኩ እየሰራ ይገኛል።

የቴክኖሎጂ እድገትና ሽግግርን ለማፋጠን ከኢንዱስትሪ ተቋማት ዪኒቨርሲቲዎች፣ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ከሀገር በቀልና የውጭ ታላላቅ ካምፓኒዎች ጋር ትስስር በመፍጠር በመስራት ላይ ይገኛል።

ተልዕኮ

·         የማምረቻ ፋብሪካዎቻችን እና ፋሲሊቲዎቻችን ዲዛይን ማድረግ እና በግንባታቸው ወቅትም በከፍተኛ የጥራት እና የኢንጂነሪንግ መስፈርቶች ብቁ ሆነው እንዲከናወኑ ማድረግ

·         የኤሌክትሪክና የኢነርጂ ፕላንቶችን ዲዛይን ማድረግ እና ከምርት እስከተከላቸው ድረስ የተዋጣላቸው አለም አቀፍ ደረጃቸው የጠበቁ ሆነው እንዲዘጋጁ ማድረግ

·         ወታደራዊ ሲስተሞችን ዲዛይን ማድረግ እና አዋጪ በሆነ ዋና ተመርተው ጥቅም የሚሰጡበትን የማምረቻ ፋሲሊቲ ተገንብቶ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ

·         ግዙፍ ድርሻ ያላቸውን ምርቶች እስከነ ማምረቻ ፋሲሊቲዎቻቸው ዲዛይን ማድረግ እና ተፈፃሚ እንዲሆኑ ማድረግ

·         የኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ፋሲሊቲዎችን ምርታማነት እና የምርት መጠን ከፍ የሚያደርጉ የሪዲዛይንግ ተግባራትን ማከናወን

ዋና ዋና ስራዎች

·         የኢነርጅ ፕሮጀክቶች የኢንጂነሪንግ ዲዛይን እና ሱፐርቭዥን ስራዎች

·         የማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ የኢንጂነሪንግ ዲዛይን እና ሱፐርቭዥን ስራዎች

·         ፕሮጀክት ዲዛይንና ዴቨሎፕመንት ስራዎች

·         ወታደራዊ ምርቶች ዲዛይን እና ዲቨሎፕመንት ስራዎች