የኮርፖሬት ትራንስፎርሜሽንና አቅም ግንባታ ማዕከል

አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ለማምረትም ሆነ ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ የሆነ አቅም ይጠይቃል። ብኢኮም ይህ በመገንዘብ የአቅም ግንባታው የሚረጋገጠው የአመለካከት ለውጥ ሲረጋገጥ መሆኑ የሚያምን ብኢኮ አመራሮችና ሰራተኞች አዳዲስ የኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ፣ የአመራርና የአመራረት ስራዎች ማቅለል የሚችሉ ልዩ ልዩ ሶፍትዌሮችና ሌሎች የቴክሎሎጂ ማኔጅመንት አጫጭር ስልጠናዎች፣ ሰሚናሮች በመስጠትና የአቅም ግንባታ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል። ማዕከሉ በተለያዩ ዘርፎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት የሰራተኞች ክህሎት በማሳደግ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ነው።

ተልዕኮ

·በብኢኮ ያሉ ጠቅላላ ስራዎች የተቀናጁ፣ጥርት ያሉ፣ስህተትን በቀላሉ ማሳየት የሚያስችሉ፣ፍጥነትን የሚጨምሩና በአጠቃላይ ምርታማነትን የሚያሳድጉ እንዲሆኑ የሚያስችሉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎችን በስፋት ያከናውናል፡፡

·በብኢኮ እስካሁን ላሉትም ወደፊት ለሚፈጠሩትም የስራ ዘርፎች ዓለማቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ  የሙያ ደረጃዎች በጥናት በተደገፈ መልኩ ያዘጋጃል፡፡

·ተፈላጊ ችሎታ፣ ዕውቀትና ስብዕና ስታንዳርዱን በጠበቀ መንገድ ማዘጋጀት፣ ሁሉም የተቋም ሰራተኞችና በተመሳሳይ ሙያ የሚሰሩ ሙያተኞችን በምዘና ብቃታቸውን በማረጋገጥ ወደ ስራ ማሰማራትና በቀጣይነትም ውጤትን እየመዘኑና ብቃትን እያረጋገጡ ማሳደግ የሚያስችል አሰራር ቀርጾ መተግበርና ወደስራ የማስገባት ስራ ይሰራል፡፡

·የኢንዳስትሪ ልማት ስራችንን ውጤት ባለው መንገድ ሊያስፈጽሙ የሚያስችሉ የተለያዩ የቴክኒክና የአመራር ዕርከኖችን ይለያል እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቦችን ያቀርባል፡፡

·የብኢኮ ሰራተኞች ዋናዎቹ የተቋሙ ብሎም የሀገር ሃብት ፈጣሪ ሃብቶች ናቸው፡፡ ስለሆነም የሰው ሃብቱ ጤንነቱ የተጠበቀ፣አስተሳሰቡ የበሰለ፣ንቁና ለስራው የበቃ እንዲሆን ማድረግ የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮች በጥናት በተደገፈ መልኩ ለአመራር አቅርቦ በማጸደቅ ተግባር ላይ ያውላል፡፡

·ሁሉም ተቋማዊ አሰራሮቻችን ስታንዳርዳይዝ በማድረግና በሂደት አፈጻጸማቸውን በመመዘንና ቀጣይነት ያለው ብሎም የተደማሪነት ውጤትን ማምጣት በሚያስችል መንገድ በማሻሻል ብክነትን ማስወገድና ተቋማዊ አፈጻጸማችንን ብሎም ምርታማነታችንን ማሳደግ የሚያስችል ስራን በከፍተኛ ሁኔታ ይሰራል፡፡

·ተቋማዊ አሰራርን በማሻሻል ይሁን አዳዲስ የሙያ ብሎም የአመራር ደረጃዎችን በመቅረጽና በመተግበር ሂደት በየደረጃው ለሚገኙ የተቋም ሰራተኞችና አመራሮች በስልጠና መልክ የማስተላለፍና አዳዲስ ለውጦችም ሲመዘገቡ በተመሳሳይ መንገድ የስልጠና ስራዎችን በመስራት ያልተቋረጠ የሰው ሃይል ዓቅም ግንባታ ስራን ያከናውናል፡፡

·ለየደረጃው የሚያስፈልጉ የዕውቀት፣ክህሎትና አስተሳሰብ መስፈርቶችንም ያዘጋጃል፤በየደረጃው ለሚመደብ ማናቸውም ሰው በተመደበበት ቦታ ብቃቱን ያረጋገጠ እንዲሆንና ስራውም ምርታማ በሆነ መንገድ እንዲሰራ ተመጣጣኝ ፈተና በማዘጋጀትና በመፈተን ብቃቱን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል፡፡